በሃገሪቱ መመሪያና ለዜጎች በሚሰጠው የመጠንቀቂያ መመሪያ መሰረት ወይም የደህንነት ችግር እደተፈጠረ በመነገሩ ፣ ወደ ስራ መድረስ ያልቻለን ሰራተኛ ከስራው ማሰናበት ክልክል ነው
በሃገሪቱ የደህንነት ችግር ምክንያት ት/ቤት በመዘጋቱ አብሮት ያለ ልጁን ለመጠበቅ ከስራ የቀረን ሰው ከስራ ማሰናበት ክልክል ነው
תקציר
በሃገሪቱ የደህንነት ችግር ምክንያት ከስራ የቀረን ሰራተኛ ከስራ ማሰናበት ክልክል ነው።
- በሃገሪቱ መመሪያና ለዜጎች በሚሰጠው የመጠንቀቂያ መመሪያ መሰረት ወይም የደህንነት ችግር እደተፈጠረ በመነገሩ ፣ ወደ ስራ መድረስ ያልቻለን ሰራተኛ ከስራው ማሰናበት ክልክል ነው።
- በሃገሪቱ የደህንነት ችግር ምክንያት ት/ቤት በመዘጋቱ አብሮት ያለ ልጁን ለመጠበቅ ከስራ የቀረን ሰው ከስራ ማሰናበት ክልክል ነው። ወይም ከሚቀጥሉት ሁኔታወች አንዱ ከተሟላ፡
- ይህ ሰራተኛ ብቻውን አሳዳጊ ወላጅ[ע] ከሆነ ወይም የልጅ ሃላፊነት በሱ ብቻ የተጣለ ከሆነ።
- የሰራተኛው ባለቤት ከስራ መቅረት የማትችል ከሆነና ልጁን መጠበቅ ካልቻለች።
- ከሰራተኛው የስራ ቦታ ወይም ከባለቤቱ የስራ ቦታ ልጁን የሚጠብቅ ከለለ።
መብቱ የሚደርሰው ማን ነው
- ሰራተኞች በሙሉ
መብቱን ለማግኘት የሚያስፈልገው ሂደት
- መብቱ ከአሰሪወች ቀጥታ መሰጠት አለበት።
- በሃገሪቱ የፀጥታ ችግር ምክንያት ስራ በመቅረት የተባረሩ ሰራተኞች አሰሪውን በቤት ዲን ለአቦዳ/ የስራ ጉዳይ ፍርድ ቤት በመክሰስ ከስራ እንዳይባረሩ፣ ወይም በህገወጥ መንገድ ስለተባረሩ አሰሪው ካሳ እንዲከፍላቸው በፍርድ ቤት መጠየቅ ይችላሉ፣ በዚህ ጊዜ ይህ ፍርድ ቤት መካስ ይችላል፣ ሰራተኝው ላይ የገንዘብ ጉዳት ባይደርስም ማለት ነው፡፡ ሰፊ መግለጫ ከስራ በመባረር ምክንያት የሚቀርብ ይግባይ[ע]።
- በዚህ አረዕስት ላይ ከስራ ከተባረረበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 12 ወራት ድረስ ክስ ማቅረብ ይቻላል።
ማወቅ የሚያስፈልገው
- በሃገሪቱ የደህንነት ችግር ምክንያት ሰራተኛን ስራ ስላልመጣ ማባረር ወንጀል በመሆኑ አሰሪው ላይ 29200 ሸቄል ቅጣት ሊያሰጠው ይችላል።
- አቅም የለላቸው ሰራተኞች፣ ያለአግባብ ከተባረሩና አማካሪና የህግ ጠበቃ ካስፈለጋቸው፣ የህግና ፍትህ እርዳታ ማግኘት ይችላሉ፣ የህግና ፍትህ መ/ቤት- እርዳታ ክፍል[ע] ፣ ለተጨማሪ መረጃወች የህግና ፍትህ መ/ቤት - የነፃ እርዳታ ክፍል[ע] ተመልከቱ።
የሚረዱ ድርጂቶች
- ስራን በተመለከተ ለሚረዱ ድርጂቶች ሰፋ ያለ ማስረጃወች ለማግነት ስራና የሰራተኖች መብቶች / እርዳታ የሚሰጡ ድርጂቶች[ע] ተመልከቱ።
የመንግስት አካሎች
ህግጋትና መመሪያወች
ሰፊ መግለጫወችና አወጣጣቸው
የተገኘው
- ይህ ትርጉም የተካሀደው ኬሬን ሀሃዳሻ ለእስራኤል በመሰረተው ሻቲል በተባለው ድርጂት እርዳት ሲሆን እንዲሁም UJC- የሰሜን አሜሪካ ይሁዳውያን ተዋህዶ ድርጂት በሰጠው እርዳታ ነው።