በዚህ ድረገፅ ማውጫ ላይ የአዳጋ ጊዜወችን ለመቋቋም የሚያስችሉ ማስረጃወችን በማሰባሰብ ለሰራተኞች፣ አሰሪወች፣ለተጠባባቂ ወታደሮችና ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም የአካል፣ የመንፈስና በንብረት ላይ ጉዳት ለደረሰባቸው ሰወች የሚያገለግሉ ማስረጃወችን አስፍረናል።

የሚያሳዝነው፣ የእስራኤል ሀገር ኑሮ አልፎ አልፎ ከህብረተሰቡ ከፊሎቹን የአዳጋ ወቅት ላይ ሲጥላቸው ይታያል።

የአዳጋ ሁኔታወች፣ ከተፈጥሮ አዳጋወች ሊደርሱ ይችላኩ (ለምሳሌ፡ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ ቃጠሎና ወ.ዘ.ተ) ወይም ደግሞ ከጦርነት (ለምሳሌ፡ ሁለተኛው የሊባኖስ ጦርነት፣ አሙድ አናንና ወ.ዘ.ተ) አዳጋወች ሊደርሱ ይችላሉ።

እነኝህ ወቅቶች ከህብረተሰቡ ብዙዉን የሚመለከቱና ተፅኖ የሚያደርሱ ናቸው፣ ብዙሃኑ ስለ አዳጋ ሁኔታወች፣ የድንጋጤ ጉዳቶች፣ የአካል ጉዳቶች፣ በንብረት ላይ ስለሚደርሱ ጉዳቶችና ወ.ዘ.ተ ላይ ጥያቄወች አሉት።

ልብ በሉ የአዳጋ ጊዜወች ሲደጋገሙ ማስረጃወች ላይ ለወጦችን ያስከትላሉ። ትክክለኛውን ማስረጃ ለመስጠት፣ የኮል-ዝኹት አባላት በእየቀኑ ማስረጃወችን እናስተካክላለን። አስፈላጊ ማስረጃ ያለው ሁሉ ሃፃአት ሺኑይ የሚለውን ቁልፍ በማስነሳት፣ እንዲሁም ቀጥታ ወደ በመግባት እንድታስታዉቁን ጥሪ እናቀርባለን።


እንዲሁም፣ በቀን አንድ ጊዜ በ www.oref.org.il የፒኩድ ሃኦሬፍ ድረገፅ በመግባት የተስተካከለ ማስረጃ ማግኘት ጥሩ ነው።

ይህ ማስረጃ ባያስፈልገን ምኞታችን ነው

ראו גם

የእርዳታ ቦታወች

  • የስልክ አገልግሎት ማዕከል ፒኩድ ሃኦሬፍ - 104 (ከማንኛውም ስልክ በነፃ መደወል ይቻላል)
  • ናታል[ע] የተባለው ድርጂት በስልክ መስመር እርዳታ ይሰጣል 1-800-363-363
  • በሽብር ፈጠራ በመጎዳታቸው ከማጠናከሪያ ቦታወች እንክብካቤ ለማድረግ የተወሰነላቸው፣ ከማንኛም የእንክብካቤ ቦታ በመሄድ፣ ወይም ከ 9፡00-15፡00 ስልክ ቁጥር -02-6709743 በመደወል እርዳታ ማግኘት ይችላሉ።

ድርጂቶችና እራሳቸውን ችለው የሚሰሩ

በአዳጋ ጊዜወች (የተፈጥሮም ሆነ የጦርነት)፣ ነጋዴወችና በግላቸው ስራ የሚሰሩ ሁሉ በስራ ሂደታቸው ላይ ችግር ይደርስባቸዋል። ከነበርው ልምድ[ע] እደሚታየው የመንግስት መ/ቤት ለምሳሌ የቀረጥ ክፍል/ራሹት ሃሚሲም ችግሩን የሚቋቋሙት ልዩ መመሪያ በማውጣት ነው። ለምሳሌ ማአም የተባለውን ተጨማሪ ቀረጥ ቆይተው እንዲከፈሉ ማድረግና ሌሎችንም መንገዶች በመጠቀም ነው።

የሚረዱ ድርጂቶች

የመንግስት አካሎች

ሰፊ መግለጫወችና አወጣጣቸው

የተገኘው

  • ይህ ትርጉም የተካሀደው ኬሬን ሀሃዳሻ ለእስራኤል በመሰረተው ሻቲል በተባለው ድርጂት እርዳት ሲሆን እንዲሁም UJC- የሰሜን አሜሪካ ይሁዳውያን ተዋህዶ ድርጂት በሰጠው እርዳታ ነው።